Skip to main content

የቤቴል 2 ሳይት የምረቃ እና የቁልፍ ርክክብ በደማቁ ተከናውኗል!

በኤማሮሽ ኢንጂነሪንግ ቃላችንን በተግባር ያሳየንበት የቤተል 2 ሳይታችን ጥቅምት 29/2018 ዓ.ል የድርጅቱ አመራሮች፣ የቤት ገዢዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል

 

ኤማሮሽ ኢንጂነሪንግ ቃላችንን በተግባር ያሳየንበት የቤተል 2 ሳይታችን ጥቅምት 29/2018 ዓ.ል የድርጅቱ አመራሮች፣ የቤት ገዢዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል። የምርቃት ፕሮግራሙ በሳይቱ አቅራቢያ ሲካሄድ የመክፈቻ እና የ እንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በ ድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሰኢድ ንጉስ አማካኝነት ቀርቧል። «27 የንግድ ሱቆችን እንዲሁም 40 የመኖሪያ ቤቶችን ለባለቤቶቻቸው ስናስረክብ እርምጃችን በዚሁ ሳይቀር ለ አዳዲስ ሳይቶቻችን ማለትም ለ ሶማሌ ተራሰባራ ባቡርአየር ጤናጀሞ እና ቤተል 3ም እየተዘጋጀን ነው።» በማለት የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሰኢድ ንጉስ በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል። አስከትለውም ተመጣጣኝ ቤቶችን በማስረከብ የሚታወቀው ድርጅቱ ኤማሮሽ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በፊት የገነባቸውን ሳይቶች እና አጠቃላይ ስለሚሰራቸው የ ኮንስትራክሽን ስራዎች በሪፖርት መልክ አንስተዋል። በስተመጨረሻም ለቤት ባለቤቶች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታቸውን አጋርተዋል።


በሁለተኛነት መልእክት እንዲያስተላልፉ የተጋበዙት የኢትዮጲያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የኤማሮሽ መስራች አደም ጓዴ የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ኡስታዝ ሐይደር ኸድር  ናቸው። እሳቸውም ለ ቤት ባለቤቶችሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ለ ድርጅቱ እንዲሁም ለአጠቃላዩ የ ሪልስቴት አልሚዎች ታማኝነታችሁን ጠብቁ የሚል አደራቸውን አስተላልፈዋል።

 

ከሪልስቴት ማህበር የምርቃት ፕሮግራሙን ለመታደም የተገኙት ምክትል ፕሬዝዳንቱ አቶ ጀበል ጀማል በበኩላቸው ብዙ ሳያወሩ 5ተኛ ሳይት ላይ መድረሱ በኤማሮሽ ኢንጂነሪንግ እንዲገረሙ እንዳስቻላቸው ገልጸው ሴክተሩ በሚታማበት በ ሪልስቴት ዘርፍ በታማኝነት መታወቁ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነም አክለዋል።  በስተመጨረሻም የ እንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ከዚሁ ከሪልስቴት ማህበር ተወካይ የሆኑት አቶ ኸድር ሰዒድም መንግስት በ5 አመታት ለመገንባት ካቀዳቸው 1.5 ሚሊየን ቤቶች ልማት ጋር አያይዘው በርቱ የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኤማሮሽ ኢንጂነሪንግ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጂነር አደም ጓዴ በበኩላቸው ለህንጻው መጠናቀቅ የላቀ አበርክቶ ያላቸውን የድርጅቱን ሰራተኞች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች ያመሰገኑ ሲሆን ለነዋሪዎቹም የ እንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ለ ልዩ ደንበኞች ደግሞ የምስክር ወረቀት እና የተወሰኑ ስጦታዎችን አበርክተዋል።

ከተጋባዥ እንድግዶች መሃል የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ መኮንን (ቴዲ ማክ) የቤቶቹን ዋጋ ከ አሜሪካ የወቅቱ የቤት ገበያ ጋር በማነጻጸር እድል ነው ሲሉ የ ኤማሮሽን ቤቶች አወድሰዋል። በዚሁ ተመጣጣኝነት እንዲቀጥል በመግለጽ ለቤት ገዢዎች መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ከእንግዶች የ እንኳን አደረሳችሁ መልእክት በኋላ የደንበኞች የምስክርነት እና የ ደስታ መልክቶችም በጉልህ ተደምጠዋል። የአከፋፈል ሁኔታው ምቹ መሆኑ፣ እውነተኛ የዋጋ ቅናሾች መኖራቸው እና ከ ሻጭ እና ገዢ በዘለለ ስላለው ቤተሰባዊነት የኤማሮሽ ቤተል 2 ቁልፍ ተረካቢዎች እንዲሁም የድርጅቱ  የበላይ ሰራተኞች ተናግረዋል።

የእለቱ የቁልፍ ርክክብ ስነስረዓትም በ ኢንጂነር አደም ጓዴ አማካኝነት ከተካሄደ በኋላ ከተጋባዥ እንግዶች እና ከ ቤተል 2 ቁልፍ ተረካቢዎች ጋር የህንጻ ጉብኝት በማከናወን በምሳ ግብዣ የእለቱ ክብረ በአል ተጠናቋል።